እኛ ማን ነን
እኛ ማን ነን!
እንኳን ወደ ONE ZERO - ዲጂታል ባንክ በደህና መጡ። ፕሮፌሰር አምኖን ሻሹዋ (Prof. Amnon Shashua) የሚቆጣጠረው ONE ZERO፣ የእስራኤል ባንክ ለመረጃ ደህንነት እና ለአደጋ አያያዝ ጥብቅ መስፈርቶችን ካሟላ በኋላሙሉ የምስክር ወረቀት የተቀበለ ሲሆን በ 2022 መጀመሪያ ላይ የባንክ ፈቃዱ ተሰጥቶታል። ONE ZERO የላቀቴክኖሎጂን በመጠቀም የገንዘብ አያያዝ ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት እና የግል የባንክ አገልግሎቶችን ለጥቂትሀብታሞች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ለማቅረብ ዓላማ ይዞ የተመሰረተ ነው። በእኛ ባለቤትነት የተያዘ የመረጃ እናደኅንነት ኤጄንሲ ላይ የተመሰረተ ቴክኖሎጂያችን፣ ለደንበኞቻችን ገንዘባቸውን የሚጠብቁ የግል እና እውነተኛ ገንዘብአስተዳዳሪዎችን እንድናቀርብ ያስችለናል። የኛ ቴክኖሎጂ በአሁኑ ጊዜ የባንክ መደበኛ ሥራ አካል ተደርጎ የሚወሰዱአሰልቺ ጊዜ የሚወስዱ፣ በእጅ የሚሠሩ ሂደቶችን በራስ ሰር እንዲሰራ ያደርጋል። በየእለቱ ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀምእያንዳንዱን አካውንት እንቃኛለን፦ ተቀማጭ ገንዘቦችን፣ ወጪዎችን፣ ቋሚ ትዕዛዞችን እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ (ad-hoc) ክፍያዎችን እንገመግማለን፣ አስፈላጊ የሆኑ ወይም ያልተለመደ እንቅስቃሴን እንለይና ለገንዘብ አስተዳዳሪዎችጥልቀት ያላቸውን ግንዛቤዎችን ማለትም ከመጠን በላይ የሆነ ወጪ ማድረግን መተንበይ፣ ድርብ የሂሳብ አከፋፈል፣ያልተሟሉ ወይም ዘግይቶ ወደ ሂሳቡ የሚደረጉ ወይም ከሂሳቡ የሚወጡ ክፍያዎች፣ ቁጠባዎችን፣ ቁጠባዎችንለማሳደግ የሚረዱ ዕድሎችን መተንበይ፣ ፋይናንስ ማድረግን፣ ግቦችን ማውጣት እና ማሳካት ያሉ ግንዛቤዎችንእንሰጣለን። የገንዘብ አስተዳዳሪዎች ግንዛቤዎቹን በመመርመር በመተግበሪያችን የጽሑፍ ልውውጥ ክፍል እናበባንክ የጥሪ ማዕከል በኩል ለደንበኞቻችን በ 24/6 አገልግሎት የምንሰጠውን ያስተላልፋሉ።
አገልግሎት እንዴት ይሰጣል?
ONE ZERO ምንም ቅርንጫፎች ሳይኖሩት፣ ዛሬ በባንኮች የሚሰጡትን ሁሉንም የባንክ አገልግሎቶች (ሞርጌጅንሳያካትት) 100% ዲጂታል በሆነ መልኩ በመተግበሪያችን በኩል ይሰጣል። የባንኩ ደንበኞች 24/6 በመተግበሪያውምሆነ በስልክ በኩል የባንክ ባለሙያዎችን ማግኘት ይችላሉ። በአሁኑ ጊዜ፣ መተግበሪያው እና የደንበኞች አገልግሎትየሚሰጡት በዕብራይስጥ ብቻ ነው፣ ነገር ግን የእንግሊዝኛ መተግበሪያ እየተዘጋጀ ነው።
የትኞቹ አገልግሎቶች በአሁኑ ጊዜ ይገኛሉ የትኞቹስ በኋላ ይታከላሉ?
በአሁኑ ጊዜ ONE ZERO ነጠላ አካውንቶችን ያቀርባል፣ በኋላ ግን፣ የጋራ አካውንቶች የሚገኙ ይሆናሉ። በአሁኑ ጊዜያሉት አገልግሎቶች፦ ዴቢት ካርዶች፣ ክሬዲት ካርዶች፣ ቼክ፣ ቋሚ የክፍያ ትዕዛዞች፣ የአካውንት ዴቢት ፈቃዶች፣የውጭ ምንዛሪ፣ የባንክ ዋስትናዎች፣ ብድሮች እና ተቀማጭ ገንዘብን ያካትታሉ። የዋስትና ንግድ አገልግሎቶች በኋላላይ ይታከላሉ። ጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ የሚደረግበት አማራጭ በኋላ ላይ ይታከላል።
ስለ ባንኩ የበለጠ መረጃ የት ማግኘት እችላለሁ?
የዕብራይስጥ ድረ-ገጻችን ስለ ባንኩ የበለጠ ጠቃሚ መረጃን ይዟል፤ የእንግሊዘኛ ንዑስ ድረ ገጽም አለ።